ሰኔ 5/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ — የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት ልማት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ11 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ተካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የዘርፉ የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ የተሳታፊዎች ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል።
"ሰልጣኞችን ከምረቃ በፊት በምዘና ብቁ ማድረግ ያስፈልጋል" — ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮርና ተቋማት ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኮሌጆች በቀሩት አጭር ጊዜያት ተመራቂ ሰልጣኞቻቸውን ከምረቃ መርኃ ግብር በፊት በምዘና ብቁ የማድረግ ሥራዎች ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተያያዘም ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ በአሰልጣኞች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ላይ የሚታዩ ክፍተቶች በአስቸኳይ እንዲስተካከሉ መመሪያ ሰጥተዋል።
በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚዴቅሳ ከበደ በበኩላቸው በውይይቱ ወቅት በሰጡት አቅጣጫ፤ ለሠራተኞች ምቹ የሥራ ሁኔታን ከማመቻቸት አንጻር ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ ተግባር መታየቱን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ ይበልጥ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በነበረው ቆይታ የልህቀት ማዕከሉ የተጀመረውን ለውጥ ተከትሎ፣ ማዕከሉ በሰው ኃይል እና በማሽነሪ ተደራጅቶ የላቀ አገልግሎት እንዲሰጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተገልጿል፤ በመድረኩም የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል።



.