Home የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትንና የዘርፉን የአመራር አቅም ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትንና የዘርፉን የአመራር አቅም ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።

15th July, 2026

ሰኔ 14/2015 ዓ.ም



የአመራር ክህሎትን በማሳደግ ተቋማዊ ተወዳዳሪነትን እና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ያለመ የ"ስትራቴጂክ ሊደርሺፕ" (Strategic Leadership) ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናውን ያዘጋጀው ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ሲሆን፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትንና የተቋማትን የአመራር አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ነው።

በዚህ ስልጠና ላይ የኮሌጅ ዲኖችና ምክትል ዲኖች፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የመጡ ተወካዮች እንዲሁም የቢሮው የስራ ኃላፊዎችና የዳይሬክቶሬቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ስልጠናው አመራሮቹ የወደፊት ዕቅዶችን በስትራቴጂክ እይታ እንዲመሩ፣ ተቋማዊ ለውጦችን በብቃት እንዲያስተዳድሩ እና በየደረጃው ምርታማነትን እንዲያሳድጉ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።


ይህ የአቅም ግንባታ መርሃ-ግብር ይበልጥ ውጤታማ እና ተደራሽ እንዲሆን በሁለት ዙር የተከፈለ ሲሆን፦
የመጀመሪያው ዙር ስልጠና ለ43 ሰልጣኞች በተሳካ ሁኔታ የተሰጠ ሲሆን፣
የሁለተኛው ዙር ስልጠና በዛሬው ዕለት በተመሳሳይ ሁኔታ በከፍተኛ ተነሳሽነት እየተሰጠ እንደዋለ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


ይህ ስልጠና አመራሩ በተግባራዊ እውቀትና በስትራቴጂክ አስተሳሰብ በመታነጽ፣ በዘርፉ የሚጠበቁ ሀገራዊና ተቋማዊ ግቦችን በብቃት ለማሳካት የበኩሉን ሚና ለመወጣት እንደሚያስችለው ይጠበቃል።

የልህቀት ማዕከሉን የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

https://pice.sims.aatvetb.edu.et/


(https://www.youtube.com/@pice1962)

(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

(https://www.tiktok.com/@pice_1962)

.

Copyright © All rights reserved.

Created with