Home የምድረ ግቢ ገጽታ ግንባታ፣ የተቋማት ልማት እና የመልካም አስተዳደር ስኬቶች

የምድረ ግቢ ገጽታ ግንባታ፣ የተቋማት ልማት እና የመልካም አስተዳደር ስኬቶች

15th July, 2026


የጥናት ምርምርና ተቋማት ልማት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የለውጥና የዕድገት ጉዞ

📌 ክፍል 1፡

በሀገራችን የትምህርትና የሥልጠና ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት እየሰራ የሚገኘው የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል፣ በ2018 በጀት ዓመት በርካታ አበይት ተግባራትን አከናውኗል። የማዕከሉ የጥናት ምርምርና ተቋማት ልማት ዘርፍ ምክትል ዲን ከአቶ ባየልኝ ጌትዬ ጋር በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የተቋማት ልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የስልጠና መሰረተ ልማት ማሻሻያ ስራዎችን በተመለከተ ሰፊ ቆይታ አድርገናል። አቶ ባዬልኝ የስልጠና ማዕከሉን ምቹና ለስራ ተስማሚ ከማድረግ አንጻር ዓመቱን ሙሉ አመራሩና ሰራተኛው በከፍተኛ ቁርጠኝነት ሲሰራ እንደነበር ገልጸው፣ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እንደሚከተለው በዝርዝር አጋርተውናል፡-

የማዕከሉን ምድረ ግቢ ምቹና ለዓይን ሳቢ የማድረግ ስራ
ማዕከሉ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ባቀደው መሠረት የምድረ ግቢውን ገጽታ የመቀየር ስራ በስፋት ተከናውኗል። በዚህም በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ምቹና ለዓይን ሳቢ እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን፣   የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ምቹ ከማድረግ አኳያ አሁን ካሉት ማቆሚያ ቦታዎች ተጨማሪ ስራዎች  ተጀምረው በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

የውሃ እጥረትን በዘላቂነት የመቅረፍ ስራ
በማዕከሉ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የነበረውን የውሃ እጥረት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ሰፊ ርብርብ ተደርጓል። ከከተማው የውሃ ልማት ቢሮ ጋር የቅርብ ትብብር በመፍጠር አዲስ የውሃ መስመር ዝርጋታ ሙሉ በሙሉ የተከናወነ ሲሆን፣ በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ወርክሾፖች (Workshops) ያለምንም መቆራረጥ የውሃ አቅርቦት እንዲያገኙ ለማስቻል የውሃ ታንከሮችን የመጠቀምና ስርጭቱን የማስተካከል ስራ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

⚽️ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ልማትና ተጨማሪ የገቢ ምንጭ
ለረጅም ጊዜ ምቹ ባልሆኑና በተለያዩ ቦታዎች ተበታትኖ ለመለማመድ ይገደድ የነበረው የማዕከሉ የእግር ኳስ ቡድን፣ ከአምናው የቀጠለ አደረጃጀትን በመከተል አሁን ላይ በማዕከሉ ግቢ ውስጥ በፓርትነርሺፕ (በአጋርነት) በለማው ዘመናዊ ሜዳ ላይ እንዲጠቀም ተደርጓል። ይህ ሜዳ ከከተማው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር ተዳምሮ የተቋሙን ገጽታ በእጅጉ የገነባ ሲሆን በተጨማሪም በማዕከሉ ውስጥ በፓርትነርሺፕ የጂምናዚየም ማዘውተሪያ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሆነ የጠቀሱት ም/ዲኑ ከማዕከሉ ሰራተኞች ባሻገር፣ ለአካባቢው ማህበረሰብም አገልግሎት እንዲሰጥ በመደረጉ ለማዕከሉ ተጨማሪ የውስጥ ገቢ ማስገኛ ምንጭ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍና የንብረት ማስመለስ ስኬቶች
አቶ ባየልኝ ጌትዬ በማዕከሉ ውስጥ ለዓመታት የቆዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍ አኳያ የተቋሙ አመራር በትኩረትና በቁርጠኝነት የሄደበት መንገድ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም፡-

የቀድሞው ልደታ ግቢ መመለስ፦ ላለፉት በርካታ ዓመታት በአካባቢው ጤና ጣቢያ ተይዞ የነበረው የቀድሞው የልደታ ግቢ፣ በአመራሩ ከፍተኛ ትግልና ቁርጠኝነት ወደ ማዕከሉ እንዲመለስ ተደርጓል። በአሁኑ ወቅትም "አፍሮ ፓድል" ከተባለ የግል ተቋም ጋር በተደረገ የጋራ ስምምነት መሰረት፣ ቦታው ላይ ዘመናዊ የፓድል ስፖርት ማዘውተሪያ ለመስራት ስራዎች እንደተጀመረ በመግለጽ አያይዘውም የሳሪስ ግቢ ከ M and M የግል ተቋም ጋር በጋራበመሆን የጋርመንት ስራ እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰዋል።


የማዕከሉን ክሊኒክ ደረጃ ማሻሻልና ማደስ፦ የማዕከሉ ክሊኒክ በነበረበት ምቹ ያልሆነ ይዞታ ምክንያት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ተነጥቆ አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረ ቢሆንም፣ በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ ክሊኒኩን በመካከለኛ ደረጃ (Medium Clinic Standard) የማደስ ስራ ተሰርቷል። በአሁኑ ሰዓትም የብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ለማስመለስ ማመልከቻ ቀርቦ ምላሹ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

ንብረቶችን ማስወገድ፦ በማዕከሉ ግቢ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተከማችተው የነበሩና ግቢውን ያጨናነቁ ቁርጥራጭ ብረቶችና የተለያዩ ንብረቶች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንብረት ግዥና ማስወገድ ቢሮ ጋር በመተባበር በግልጽ ጨረታ እንዲሸጡ ተደርጓል። በዚህም አሸናፊ ለሆኑ ተጫራቾች ንብረቱ ተላልፎ የተሰጠ ሲሆን፣ ወደ  3,556,000 (ሦስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ) ብር ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

(የወርክሾፖችን አደረጃጀት፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ማሽኖችን ማሟላትና ታሪካዊውን የ ISO ዓለም አቀፍ የጥራት እውቅና ስኬት የተመለከተው የቃለ መጠይቁ ሁለተኛ ክፍል ይቀጥላል... ከእኛ ጋር ይቆዩ!)

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/@pice1962)

Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/@pice_1962)

.

Copyright © All rights reserved.

Created with