Home Rበልህቀት ማዕከሉ የሥራ ፈጠራ ክህሎት ውድድር ተካሄደ።

Rበልህቀት ማዕከሉ የሥራ ፈጠራ ክህሎት ውድድር ተካሄደ።

24th January, 2026

ሕዳር 19/2018ዓ.ም 

ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ በቴክኖሎጂ ልማት ኢንኩቤሽን ስር የቢዝነስ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ግለሰቦች መደገፍ አንዱ ሲሆን በዚህም የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን በዛሬው ዕለት  የፈጠራ ሀሳባቸውን አቅርበው አብራርተዋል፡፡

  በዚህ የውድድር መድረክ ላይ የማዕከሉ የቴክኖሎጂ ልማት ኢንኩቤሽን አገልግሎት ም/ዲን የሆኑት አቶ ተስፋዬ ወርቁ መድረኩን የመሩ ሲሆን በተጨማሪም ለተወዳዳሪዎች የልህቀት ማዕከሉን ተግባር አጠር ባለ መልኩ በመግለጽ የእለቱን የውድድር መድረክ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ የአ.አ ስራና ክህሎት ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ኢንኩቤሽን አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ፀጋዬ በየነን  ወደመድረክ ጋብዘዋል።

ውድድሩ አዲስ የቢዝነስ ሀሳብን አልምቶ ወደ ገበያ ለማስገባት የሚያስችል አቅም እንዳለውና ለከተማው ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት በመግለፅ ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሀሳባቸውን አቅርበው ለሚልፉ ተወዳዳሪዎች የአ.አ.ከ ስራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል እንደሚደግፍ አቶ ፀጋዬ በየነ ጠቅሰዋል።

በመቀጠልም የቢዝነስ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ይዘው የመጡትን ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ከቀረቡት 9 የፈጠራ ሃሳቦች ውስጥ በጥቂቱ 

1- Bagasse fly ash for industrial wastewater treatment 

2-Upcycled bags, rugs, and shoes

3-Essential oil extraction from coffee waste, lemon peel, herbs

የሚሉ የመወዳደሪያ ሀሳቦች ይገኙበታል።

 በመጨረሻም የማዕከሉ ዋና ዲን የሆኑት አቶ አድማሱ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ ዳኞች በሚሰጡት ነጥብ መሠረት አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ወደ ልህቀት ማዕከሉ ግቢ ውስጥ በመግባት የኢንኩቤሽን ስራ እንደሚሰሩ  በመጠቆም ይሄን ስራ በሀላፊነት እየሰሩ ለሚገኙ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with