(ክፍል አንድ)
🇪🇹አዲስ አበባ | መጋቢት 2018 ዓ.ም🇪🇹
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግረውን አዲሱን ስትራቴጂ ወደ ተግባር በማሸጋገር፣ የ2017 ዓመትን "ከፍታን ማጽናት ነገን የማላቅ" ዘመን አድርጎ እየሰራ ይገኛል። በዚህ ስትራቴጂካዊ ጉዞ ውስጥ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የምርታማነትና ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል፣ ተቋማዊ ትራንስፎርሜሽንን በተግባር በማሳየት ላይ ነው።
የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ከአዲሱ ስትራቴጂ ጋር ተያይዞ ተቋሙ እያከናወናቸው ስላሉት "ማርሽ ቀያሪ" ስራዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
"ከዳቦ በላይ"፦ የሰው ሃይልን የማብቃት አዲስ መርህ
አቶ አድማሱ እንደሚሉት፣ አዲሱ ስትራቴጂ ማርሽ ቀያሪ የተባለበት ዋና ምክንያት ነባሩን የስልጠና አረዳድ ስለቀየረው ነው። "ከዳቦ በላይ" የሚለው መርህ ስልጠናዎች የዕለት ጉርስን ከመሸፈን አልፈው፣ ሰልጣኞች ለሌሎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩበትን እና ሀገርን መመገብ የሚችሉበትን አቅም የሚፈጥሩ ናቸው። ይህ እሳቤ በውስጡ 11 የክህሎት-መር (DNA) እሳቤዎችን የያዘ ሲሆን፣ ማዕከሉ እነዚህን እሳቤዎች በስሩ ባሉት 14 ኮሌጆች ውስጥ ተግባራዊ እዲሆኑ የመደገፍ ስራ ጀምሯል፡፡
ዲጂታላይዜሽን (Digitalization)፦ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና ማዕከሉ በግንባር ቀደምትነት ከያዛቸው ስራዎች አንዱ ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማብቃት ነው። ለዚህም፦ Virtual Reality (VR)፦ በከፍተኛ በጀት ተገዝተው አቧራ የሚለብሱ ማሽኖችን በመተካት፣ በምናባዊ እውነታ (Virtual Reality) የታገዘ ዘመናዊ ስልጠና ለማስጀመር ቅደም ዝግጅት ስራ አጠናቅቆ ወደ ተግባር ምዕራፍ እየተሸጋር ይገኛል፡፡ ይህም ሰልጣኞች ከዘመናዊው የዲጂታል ዓለም ጋር በቀጥታ እንዲቀላቀሉ ያደርጋል።
ፈር ቀዳጅነት፦ ማዕከሉ ራሱ ዲጂታል በመሆን በስሩ ያሉ ሌሎች ኮሌጆችም ወደዚህ አሰራር እንዲገቡ የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።ተቋማዊ ኢንተርፕሪነርሽፕ (Public Entrepreneurship)
ተቋሙ ስልጠና መስጠት ብቻ ሳይሆን፣ ራሱም ገቢ የሚያመነጭ "ኢንተርፕሪነር" መሆን እንዳለበት ስትራቴጂው ያስገድዳል።
በዚህም መሠረት፦
ስያሜና ህጋዊ ማዕቀፍ፦ ማዕከሉ ስሙን ወደ "የኢንተርፕሪነርሽፕና የቴክኒካል ስክክ የልህቀት ማዕከል" (Entrepreneurship & Excellence of Technical Skill Center) ለመቀየር አዲስ ደንብ አዘጋጅቶ በካቢኔ ለመጽደቅ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
ተጨባጭ የንግድ ስራዎች (PLC)፦ ተቋሙ በራሱ ግቢ ውስጥ 7 የሚጠጉ የንግድ ፈቃዶችን አውጥቶ ወደ ስራ ገብቷል። የአዲስ አበባ ምክር ቤት ጽህፈት ቤትን፣ የፕላንና ልማት ቢሮን እንዲሁም የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልን ሙሉ ፈርኒቸር በማምረት እና ቢሮዎችን በማደስ ከፍተኛ ገቢ በማግኘት በጀቱን ደጉሟል። ዘርፈ-ብዙ አገልግሎት፦ በአውቶሞቲቭ ዘርፍ የመኪና ጥገና እና የሾፌሮች ብቃት ማሻሻል፣ በብረታ ብረት ዘርፍ ደግሞ የዶሮ ኬጆችን በማምረት የገበያ ክፍተቶችን እየሞላ ይገኛል።
የኮሌጆች ድጋፍና የቴክኖሎጂ ሽግግር
ማዕከሉ በየዓመቱ በኮሌጆች ተሰርተው የተቀመጡ ቴክኖሎጂዎች ከግቢ ወጥተው ወደ ገበያ እንዲገቡ ኃላፊነት ወስዷል። ለዚህም አንድ ልዩ ቡድን ተቋቁሞ በየኮሌጆቹ የተሰሩ አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን በመለየት፣ በማዕከሉ እንዲመረቱ (Fabricate) እና ለገበያ እንዲቀርቡ የመሸጫ ቦታዎችንም አዘጋጅቷል። ለዚህ ስራ ስኬት የሥራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ በጀት መድቦ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አቶ አድማሱ ገልጸዋል።
በቀጣይ ክፍል (ክፍል ሁለት)፦
ስለ አዲሱ ስትራቴጂ ቀሪ መርሆዎች፣ ስለ "Renovation" ስራዎ





.