#የልህቀት_ማዕከሉ_ተልዕኮውን_ከማሳካት_አንጻር_የሚበረታታ_ስራ_እየተሰራ_እንደሆነና_ምቹ_የስራ_ቦታን_ለመፍጠር_የተሄደበት_ርቀት_የሚደነቅ_ነው
24th January, 2026
#የልህቀት_ማዕከሉ_ተልዕኮውን_ከማሳካት_አንጻር_የሚበረታታ_ስራ_እየተሰራ_እንደሆነና_ምቹ_የስራ_ቦታን_ለመፍጠር_የተሄደበት_ርቀት_የሚደነቅ_ነው"
አቶ አድማሱ በቀለ (የማዕከሉ ዋና ዲን)
ታኅሳስ 27/2018 ዓ.ም
ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል በዛሬው ዕለት በ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ ክንውን ግምገማ እንዲሁም ውይይት ሲያካሂድ ቆይቷል።
የልህቀት ማዕከሉ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸው ተግባራት ሪፖርት ያቀረቡት የእቅድና በጀት ግምገማ ክትትል ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ ሉሊት ካሳሁን ሲሆኑ በሪፖርታቸውም የዓበይት ተግባራት አፈፃፀም በሚል :- ከአቅርቦት መር ወደ ፍላጎት መር ፣ ማዕከሉን ለስልጠና ምቹና ሳቢ ከማድረግ ፣ የምርምር ፈጠራና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም ችግር ፈቺ ክትትልና ድጋፍ ፤ ዘመናዊ የመረጃ አደረጃጀት ማሳደግ በሚል በጥንካሬ የተሰሩ ስራዎችን አንስተዋል።
በመቀጠልም የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ቤቱ ሀሳብ አስተያቱን እንዲያነሳ እድል የሰጡ ሲሆን በዚህም ከቤቱ በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች መሠረት በሪፖርቱ ፓወር ፖይንት መካተት ይገባቸው ነበር ያሏቸውን ማዕከሉ ያከናወናቸውን ተግባር በማንሳት ሊበረታታ ይገባል ያሉ ሲሆን መስተካከል የሚገባቸውን እንዲሁም መሰራት አለበት ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል።
በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች በየ ዘርፉ ያሉ የማዕከሉ ምክትል ዲኖች ከግልጸኝነት አንጻር ያከናወኗቸውን ተግባራት ከጥያቄና አስተያየቶቹ ጋር በማስማማት ምላሾቻቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም አቶ አድማሱ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር አገልግሎትን ከማሻሻል አንጻር ተቋማዊ ግንባታ ስርዓት በመዘርጋት የሰራተኛውን የመፈፀም አቅም በማሳደግና ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር ማዕከሉ የሄደበት ርቀት የሚደነቅ እንደሆነና የሚታይ ለውጥ እየመጣ እንደሆነ በመግለጽ የተነሱ ሀሳቦችም ለቀጣይ ስራዎች ስንቅ ይሆናል በማለት መሻሻል የሚያስፈልጋቸው ተግባራት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)
YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/@pice1962)
Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)
TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/@pice_1962)




.