Home " የምርታማነትና ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል አዲስ ስኬት" (ክፍል አራት)

" የምርታማነትና ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል አዲስ ስኬት" (ክፍል አራት)

07th April, 2026

🇪🇹አዲስ አበባ | መጋቢት 13/2018 ዓ.ም🇪🇹 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ተክለማርያም ጃታና፣ ከምርታማነትና ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ማዕከሉ ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የሚነሱ ቅሬታዎችንና የተመዘገቡ ስኬቶችን በሚመለከት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የኮሌጆች ቅሬታና የ"ብቃት" ምላሽ አንዳንድ ኮሌጆች ከማዕከሉ የሚፈልጉትን ድጋፍ ልክ እንደማያገኙ ለሚነሳው ቅሬታ አቶ አድማሱ ሲመልሱ፤ "ቅሬታው ትክክል ነው፣ ጥናታችንም ያረጋገጠው ይሄንኑ ነው" ብለዋል። ችግሩ የመደገፍ ፍላጎት ማጣት ሳይሆን፣ ማዕከሉ እንደ ስሙ 'የልህቀት ማዕከል' ሆኖ ለመገኘት በሰው ኃይልና በማሽነሪ ረገድ የነበረበት የአቅም ክፍተት መሆኑን ገልጸዋል። 

ይህንን ክፍተት ለመሙላት ማዕከሉ ሁለት ዋና ዋና መፍትሄዎችን እየተገበረ ይገኛል፦

የሰው ኃይል ግንባታ፦ አቅም ያላቸው አዲስ ባለሙያዎችን መቀጠርና ነባሮቹን ደግሞ 'Wholistic' በተባለው አዲስ የምዘና ሥርዓት ብቁ እንዲሆኑ በማድረግ የኮሌጆችን አሰልጣኞች መደገፍ የሚያስችል አቅም መፍጠር። 

የማሽነሪዎች ሽግግር፦ ጊዜ ያለፈባቸውን (Outdated) ማሽኖች በዘመናዊ የዲጂታል ማሽኖች በመተካት ኮሌጆች የሚፈልጉትን ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻል።

የፋይናንስ ተዓምር፦ ከ1.5 ሚሊዮን ወደ 10 ሚሊዮን ብር በአዲሱ ስትራቴጂ "ስልጠና በላይ" በሚለው እሳቤ መሠረት፣ ተቋሙ ከመንግስት በጀት ጥገኝነት ወጥቶ ራሱን እንዲችል ሰፊ ስራ ተጀምሯል። 

አቶ አድማሱ እንደገለጹት፣ ማዕከሉ ቀደም ባሉት ዓመታት በዓመት ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማመንጨት አይችልም ነበር። አሁን ግን በስድስት ወር ውስጥ ብቻ 10 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማመንጨት ችሏል።

ይህ ስኬት የተመዘገበው፦

እንደ 2markato.com ባሉ የዲጂታል ገበያ (Digital Marketing) አማራጮች ራስን በማስተዋወቅ፤

በመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት (e-GP) ላይ እንደ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ተመዝግቦ በጨረታዎች መሳተፍ በመጀመሩ፤የገቢ ምንጮችን በማብዛትና የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል መሆኑ ተገልጿል።

አጋርነት ለምርታማነት፦ የጂምናዚየም እና የሜዳ ግንባታ

ማዕከሉ ከባለሀብቶች ጋር ባደረገው አጋርነት (Partnership) ለሰራተኞች ምቹ የሥራ ሁኔታን ፈጥሯል። 

ለ225 ሰራተኞች አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ጂምናዚየምና የስፖርት ሜዳ በፓርትነርሺፕ እንዲገነባ ተደርጓል። ይህም የሰራተኞችን ጤና ከመጠበቁና ምርታማነትን ከመጨመሩ ባለፈ፣ ለተቋሙ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መሆን መጀመሩ ተጠቁሟል።

በቀጣይ ክፍል (ክፍል አምስት - የመጨረሻ) የሚመለሱ ነጥቦች፦

ባለሀብቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ዋጋ ያላቸውን ማሽነሪዎች በማዕከሉ ውስጥ መትከል የጀመሩት ለምንድነው?

አንድ የፈጠራ ባለሙያ (Incubatee) በ "30/70" የትርፍ ክፍያ ሞዴል ከማዕከሉ ጋር እንዴት እየሰራ ይገኛል?

አዲሱ ስትራቴጂ የ"መጠበቅና የጥገኝነት" መንፈስን እንዴት ሰበረው?

የቃለ-ምልልሱ የመጨረሻ ክፍል በቅርብ ሰዓት ይጠብቁን።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with