Home "የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልፅግና"፤ የ16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ኤግዚቢሽን በልህቀት ማዕከሉ በድምቀት ተከፈተ።

"የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልፅግና"፤ የ16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ኤግዚቢሽን በልህቀት ማዕከሉ በድምቀት ተከፈተ።

01st May, 2026

🇪🇹አዲስ አበባ | ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም🇪🇹 

"የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ የሚገኘው 16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አካል የሆነው የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን በምርታማነትና ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል (PICE) ተከፍቷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ፤ ማዕከሉ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት እንደ ዋና የልማት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ገልጸዋል። 

ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በንግግራቸው፤ የአንድ አገር ቀጣይነት ያለው እድገት የሚረጋገጠው በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በፋይናንስ ዘርፎች መካከል የተቀናጀ ትስስር ሲኖር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተደረገው ርብርብ በአዲስ አበባ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የምርታማነት ደረጃ ከነበረበት ከ40-50 በመቶ ወደ 70 በመቶ ከፍ ማለቱን ጠቁመዋል። 

ኃላፊው አክለውም፣ መንግስት ለጀማሪ ኢንዱስትሪዎች (Infant Industries) እንደ ህጻን ልጅ ልዩ እንክብካቤና የፖሊሲ ጥበቃ ሊያደርግ እንደሚገባ ገልጸው፤ ይህም አገር በቀል እውቀትንና ዲጂታል አቅምን ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጋር በማቀናጀት (Smart TVET) የሚረጋገጥ መሆኑን አስረድተዋል። 

በአዲስ አበባ የኢትዮጵያን 40 በመቶ የኢንዱስትሪ ድርሻ የያዘች ከተማ በመሆኗ፣ ይህ የልህቀት ማዕከል ከ14ቱ የከተማዋ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ይጠበቃል። የከተማ አስተዳደሩም ለተቋሙ መጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ አረጋግጠዋል። 

የማዕከሉ ዲን አቶ አድማሱ በቀለ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ ከተለመደው የቴክኖሎጂ መቅዳት (Copying) ዑደት ወጥቶ ወደ ተከታታይ ምርት (Mass Production) መሸጋገሩን አብስረዋል። 

በተለይም የ"ወርቅ አፈር ማጠቢያና መለያ ማሽን" ከፕሮቶታይፕ ደረጃ አልፎ ትዕዛዞች እየተቀበለ መሆኑንና ይህም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ በተግባር የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል። 

በኤግዚቢሽኑ ላይ የዘመን ባንክ፣ ስኬት ባንክና ብርሃን ባንክ አመራሮች መገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ እነዚህ ተቋማት ለአምራች ዘርፉ የሚያደርጉት ድጋፍ አገርንና ትውልድን የመገንባት ስራ መሆኑ ተመልክቷል። በተጨማሪም በማዕከሉ ውስጥ ለረጅም ዘመናት ልምድ ያካበቱ አንጋፋ ባለሙያዎች እውቀታቸውን ለቀጣዩ ትውልድ እንዲያስተላልፉና ተቋሙ የኢንተርፕረነርሺፕ ማዕከል እንዲሆን ይሰራል ተብሏል።

#ጥበብና_ልህቀት

የዕለቱን መድረክ ያስዋበችልን ሰኒ ዲኮር 🙏

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....

https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962

(https://www.youtube.com/@pice1962)

Facebook Channel ………….PICE

(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962

(https://www.tiktok.com/@pice_1962)

.

Copyright © All rights reserved.

Created with