የማዕከሉ ጠቅላላ ሰራተኞች የወርቃማው ሰኞን ልምምድ ወደ ማዕከሉ ለማምጣት በተዘጋጀው የመጀመሪያው የአብሮነት መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
የመርኃ- ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከሉ ዋና ዲን #አቶ_አድማሱ_በቀለ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ማዕከሉ ይህንን የወርቃማ ሰኞ ልምድ ልውውጥን ለመጀመሪያ ጊዜ ማስጀመሩን የገለጹ ሲሆን አያይዘውም ይህ የወርቃማው ሰኞ የአብሮነት መድረክ በየሳምንቱ ሰኞ ሰኞ ለአጭር ደቂቃ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡
በመቀጠልም የ2018 የመጀመሪያ በጀት ዓመት ወርቃማው ሰኞ የአብሮነት መድረክ ላይ ስልጠና የሰጡት የማዕከሉ የአቅም ግንባታ ም/ዲን #አቶ_ተሾመ '' Ignite Your Potential: An Inspirational Journey for Our Team'' በሚል ርዕስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና የሰጡ ሲሆን በዚህም ለጋራ ራዕያችን እምቅ ችሎታችንንና ኃይላችንን እንዴት ማበርከት አለብን በማለት ዝርዝር ገለጻ ለሰራተኛው ሰጥተዋ በተጨማሪም የወርቃማው ሰኞ እንቅስቃሴ ከራስ ልምድና ተሞክሮ በማዋዛት ዘወትር ሰኞ በተከታታይነት ተቋማዊ ግንዛቤን በመጨመር እና ለተቋም ራዕይ መሳካት ጉልህ ሚና አለው ያሉ ሲሆን በስራ ውጤታማ ለመሆን ራስን መግዛት ጥቅሙ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰው ሰራተኞች የስራ ባህላቸውን ለማሳደግና የሚገጥማቸውን ችግሮች በውይይት በመፍታት ወደላቀ ስኬት ለማድረስ ወርቃማ ሰኞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡
በመጨረሻ ማዕከሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያስመዘገበ ላለው ውጤት ለማዕከሉ ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ነሃሴ 5/2017 ዓ.ም
ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል








.