ጥቅምት 10/2018 ምርታማነት ማሻሻያየልህቀት ማዕከል
በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ባስመዘገቡ የሥራ ክፍሎች እና ባለሙያዎች የላቀ ተነሳሽነትና መቀራረብን በማበረታታት መርህ የእውቅና እና የአብሮነት ፕሮግራም አካሂዷል።
በቁልፍ እና አበይት አመላካች ግቦችን በማሳካት፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ የፈጠራ ሥራዎችን በማቅረብ፣ እንዲሁም የተግባራዉ ጥናትና ምርምር ስራ የላቀ አስተዋጽኦ በማበርከት የላቀ ውጤት ላመጡ የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች የምስክር ወረቀቶች፣ ዋንጫዎች እና ልዩ ልዩ ሽልማቶች ተበርክተዋል። ሽልማቱም የክፍሎቹንና የባለሙያዎችን ጠንካራ የስራ ባህልና ውጤታማነት ለማድነቅ እና ለቀሪዎቹም አበረታች ምሳሌ ለመሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ።
መጨረሻም የልህቀት ማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ተቋማችን ያስመዘገበው ስኬት የሁላችንም የጋራ ጥረት ውጤት ነው። ዛሬ እውቅና የተሰጣቸው የስራ ክፍሎች እና ባለሙያዎች ላሳዩት የላቀ አፈጻጸም፣ ቁርጠኝነት እና የላቀ ተነሳሽነት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የእውቅና እና የአብሮነት ፕሮግራሙ የማዕከላችንን የላቀ የስራ ባህል እና ሰራተኞችን የማድነቅ መርሆችን የሚያሳይ በመመሆኑ ይህ አይነቱ ፕሮግራም በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዲኑ ገልጸዋል።











.