የልህቀት ማዕከሉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሃሴ 9 ቀን 2017ዓ.ም በወጣው የግልጽ ጨረታ ውድድር ላይ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 4:00ሰዓት ዘግቶ ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች በተገኙበት በግልጽ ተከፍቷል።
የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ በጨረታ መክፈቻ መርኃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታን በይፋ ያስከፈቱ ሲሆን ለተወዳዳሪዎች መልካም እድል እንዲገጥማቸው በመመኘት ጨረታውን አስጀምረዋል።
በመቀጠልም ከተጫራቾችና ከማዕከሉ ታዛቢዎች ሳጥኑ የታሸገ መሆኑን አረጋግጠው የከፈቱ ሲሆን የጨረታ ሂደቱን በግልጽ በመከታተል ላይ ይገኛሉ።
በጨረታው ላይ የማዕከሉ ዳይሬክቶሬቶች በታዛቢነት መከታተላቸውን ተመልክተናል።
ነሃሴ 23/2017 ዓ.ም
The Center of Excellence opened openly at 4:00 am today in the presence of bidders at the open auction competition published in Addis Ababa newspaper on August 9, 2017.




.