Home ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የ2018 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርን በታላቅ ስኬት አከናወነ

ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የ2018 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርን በታላቅ ስኬት አከናወነ

15th July, 2026

[አዲስ አበባ]ሰኔ 29/2018ዓ.ም
የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የአካባቢ ጥበቃንና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን አገራዊ ጥረት በመደገፍ፣ የ2018 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብሩን በዛሬው ዕለት በልዩ ንቅናቄ አካሂዷል።

በማዕከሉ ግቢና በአካባቢው በተከናወነው በዚህ መርሀግብር ላይ የማዕከሉ አመራሮችና ሰራተኞችን ጨምሮ በአጠቃላይ 240 የሚሆኑ የማዕከሉ ማህበረሰብ አባላት በንቃት ተሳትፈዋል።

ከአረንጓዴ ልማት እስከ ምርታማነት

የአረንጓዴ አሻራ ማለት ተፈጥሮን የመንከባከብ፣ የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም እና ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች አረንጓዴ ፕላኔትን የማስረከብ የጋራ ቃልኪዳን ነው። ይህ መርሀግብር ዛፎችን በመትከል አካባቢን ከማልማት ባለፈ፣ የሀገርን ምርታማነት በማሳደግ፣ የስነ-ምህዳር መመጣጠንን በመጠበቅና ምግብ ነክ የሆኑ ተክሎችን በመትከል የኢኮኖሚ አቅምን ለመገንባት ትልቅ ሚና ይጫወታል። ማዕከሉም ይህንን አገራዊ ጥሪ መሰረት በማድረግ ነው አሻራውን ያኖረው።

የችግኝ ተከላው ዝርዝር መረጃ

በዕለቱ የተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሀግብር በግቢ ውስጥ እና ከግቢ ውጭ ባለ አካባቢ  በሚሉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን፣ የተተከሉት የዕፅዋት ዓይነቶችና የሸፈኑት የቦታ ስፋት ስንመከት:-
በማዕከሉ ግቢ ውስጥ፦ ውበትንና የምግብ ዋስትናን ታሳቢ ባደረገ መልኩ 2300 ካሬ ሜትር በሚጠጋ ስፋት ላይ የፍራፍሬ እና የአበባ አትክልቶች ተተክለዋል። ከእነዚህም የአቮካዶ ፍራፍሬ ተክሎች እንደሚገኙበት ታውቋል።

ከማዕከሉ ግቢ ውጪ፦ የአካባቢውን የአየር ንብረት ለመጠበቅና ጥላ ለመፍጠር 5293 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ቦታ ላይ 935 የጥላ ዛፎች በስኬት ተተክለዋል።
በጠቅላላው ማዕከሉ 1590 የተለያዩ የችግኝ አይነቶች መትከሉን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህ የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ያከናወነው አረንጓዴ አሻራ፣ ተቋሙ ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት ከማሳየቱም በላይ ለአረንጓዴ ልማት ግንባታ አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/@pice1962)

Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/@pice_1962).

Copyright © All rights reserved.

Created with