Home የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

15th July, 2026

ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም

ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል በዛሬው ዕለት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን ግምገማ እና የጋራ ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ማዕከሉ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በሪፖርት መልክ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በሪፖርቱ ይዘት የተካተቱ ነጥቦች:- ማዕከሉ የተጣለበትን ተልዕኮ ከመወጣት እና ስራዎችን ከማሳካት አንጻር አበረታች ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል በተጨማሪም  ለሰራተኞች እና ለባለድርሻ አካላት ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር የተሄደበት ርቀት እና የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት የሚደነቅ እንደሆነ ተመላክቷል።

በቀረበው ሪፖርት ዙሪያም ውይይት ከተካሄደ በኋላ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች፣ በየዘርፉ ያሉ የማዕከሉ ምክትል ዲኖች  ግልጽነት ባለው መልኩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዚህም ማዕከሉ በበጀት ዓመቱ ያሳያቸውን ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጠናከር እና የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በጋራ ለመስራት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ አጠናቀዋል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

(https://t.me/pice1962)

PICE1962
(https://www.youtube.com/@pice1962)

Facebook Channel
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok
Pice_1962
(https://www.tiktok.com/@pice_1962)

.

Copyright © All rights reserved.

Created with