Home ሳምንታዊ ወርቃማ ሰኛ መድረክ እና የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተከናወነ። መስከረም 26 2018 ዓ.ም ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል።

ሳምንታዊ ወርቃማ ሰኛ መድረክ እና የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተከናወነ። መስከረም 26 2018 ዓ.ም ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል።

10th October, 2025

የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ሳምንታዊ ወርቃማ ሰኛ የዕውቀት ሽግግር መድረክ እና ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ። 

ዘወትር በየሳምንቱ የሚካሄደው የወርቃማው ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መድረክ ዛሬም ቀጥሎ የቀረበ ሲሆን Teams work like a geese በሚል ዕሳቤ በማዕከሉ  አሰልጣኝ አቶ አብረሃም ተስፋዬ የቀረበ ሲሆን አሰልጣኙ የ geese ባህሪን እና የአኗኗር ዘይቤን እንዴት ወደ ተቋማችን በማምጣት በጋራ እና በትብብር ሰርተን ለውጥ ማምጣት እንዳለብን ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። 

በመቀጠል የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ኢንኩቤሽን አገልግሎት ም/ዲን አቶ ተስፋዬ ወርቁ የማዕከሉን የሶስቱንም ዘርፍ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን ሪፖርቱን በዕቅድ እና ክንውን፣ በትግበራሂደት ያጋጠሙ ችግሮች እና የተፈቱበት አግባብ፣ እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት መስኮችን በሚል ዘርዝረው አቅርበዋል። አክለውም እያንዳንዱ ሰራተኞ የማዕከሉን ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዕሴቶቹን በደንብ ማወቅ እንደሚገባም አፅንዖት ሰጥተው ገልፀዋል። 

የዕቅድ አፈፃፀሙን መነሻ በማድረግ ከማዕከሉ ሰራተኞች ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በተለይ የማዕከሉ ህንፃ ሲሰራ ለአካል ጉዳተኞ ምቹ ባለመሆኑ ያንን ታሳቢ ያደረገ በተለይ በከተማ ደረጃ እየተተገበረ እንዳለው እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በህንፃው ግራውንድ ላይ እንዲጀመር የሚል እና ሌሎች ሪፖርቱን የሚያዳብሩ  ሀሳብ ቀርበዋል። 

በመቀጠል ከመድረክ የተነሱትን ሀሳቦች በየደረጃው ያሉ የማዕከሉ ም/ዲኖች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተለይ ምላሽ መስጠት የሚችሉትን ጥያቄዎች የዕቅድ አካል ተደርገው ቶሎ እንደሚመለሱ እና አሰራር እና መመሪያን ብቻ ተከትለው የሚሰሩትን ደግሞ በመመሪያው ብቻ ምላሽ እንደሚያገኙ ግልፅነትን ፈጥረዋል። 

በመጨረሻም የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ እንደተናገሩት እንደወርቃማ ሰኞ ዓይነት መድረኮች ሰራተኞችን ይበልጥ እንደሚያቀራርቡ እና አዳዲስ ልምዶችን እና ዕውቀቶችን እንደሚያስገኙ የገለፁ ሲሆን፤ በመቀጠል በሩብ ዓመቱ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ነገር ግን አጠር ተደርገው ለመድረኩ እንደቀሩ በማሳወቅ ቀሪ ስራዎችን በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንደሚገባ እና ሁል ጊዜ ለውጥን መናፈቅ እንዳለብን እና ለዚያም መዘጋቸት እንዳለብን በጥብቅ ያሳሰቡ ሲሆን፤  በተለይ አሰልጣኞች በአዲሱ የሙያ ብቃት ምዘና ተመዝነው መብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል። 

የመረጃ ምንጭ:- በዕለቱ ከተከናወነው መድረክ የተገኘ!!!

.

Copyright © All rights reserved.

Created with