ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል።
በየሳምንቱ ሰኞ በሚያካሂደው "ወርቃማ ሰኞ" የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ላይ፣ የልህቀት ማዕከሉ ዋና ዲን የሆኑት አቶ አድማሱ በቀለ ቀዳሚነትን/ንቁነትን (Proactive) የሥራ ባህል ስለማድረግ አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ሰፋ ያለ ሥልጠና ሰጡ።
የሥልጠናው ዋና ትኩረት ሠራተኞችና አሰልጣኞች ከምላሽ ሰጪነት (Reactive) ወደ ንቁና ለውጥ አምጪነት (Proactive) የአስተሳሰብ ዘይቤ እንዲሸጋገሩ ማስቻል ነው። ይህም የማዕከሉን ምርታማነትና አገልግሎት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ነው።
ዋና ዲኑ በስልጠናው ወቅት እንዳብራሩት፣ ንቁ አስተሳሰብ በሥራ ላይ ሲተገበር የሚያስገኛቸውን ዋና ዋና ጥቅሞች የዘረዘሩ ሲሆን፦
• ጊዜንና ጉልበትን መቆጠብ: "ንቁ የሆኑ አሰልጣኞች/ሠራተኞች ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ይተነብያሉ፤ በዚህም ድንገተኛ ቀውሶችን ለመፍታት የሚባክነውን ጊዜና ጉልበት ይቀንሳሉ።
• ለለውጥ ዝግጁነት: ቀዳሚነትን መውሰድ የሥራ አካባቢን አስቀድሞ በመገንዘብ፣ ማዕከሉ ከአዳዲስ ሁኔታዎች ጋር በቀላሉ እንዲላመድና በዘርፉ መሪነቱን እንዲያረጋግጥ ያግዛል።
• የላቀ ውጤት ማስመዝገብ: ንቁ ሠራተኞች ውጤትን ለመጠበቅ ሳይሆን ውጤት ለመፍጠር ስለሚሰሩ፣ ይህ የማዕከሉን አጠቃላይ ምርታማነት ከፍ በማድረግ በላቀ ደረጃ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችለዋል፣በተለይ በማሠልጠኛ ዘርፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ አሰልጣኞችም ይህንን አስተሳሰብ ለሰልጣኞቻቸው እንዲያሰርፁ አሳስበዋል።



.