ኅዳር 2/2018 ዓ.ም
በምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ በፀረ ሙስና ህጎቸ፣ አዋጆችና መመሪያዎች እንዲሁም ግብረ ግብረ ገብነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለማዕከሉ ሰራተኞች የሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይ ከሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በመጡ ባለሙያ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡
በዚህም በስልጠናው ላይ የተለያዩ ርዕሶች የተነሱ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል፡- የምግባር ምንነት፣ ግብረገባዊ ግዴታዎች፣ የግብረ ገብ እሴት ማዳበር ዓላማው፣ እንዲሁም የአመራርና የሰራተኞች ግብረ ገብ ምን መምሰል አለበት በሚሉ ዙያዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡
ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል



.