Home የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የISO 21001:2025 ዓለም አቀፍ የጥራት ሰርተፍኬት አገኘ፡፡

የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የISO 21001:2025 ዓለም አቀፍ የጥራት ሰርተፍኬት አገኘ፡፡

21st February, 2026

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ
🇪🇹  የካቲት  13 /2018 ዓ.ም🇪🇹 

በሀገራችን የትምህርትና የሥልጠና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የምርታማነት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል  በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያውን የISO 21001:2025 (Educational Organizations Management System - EOMS እውቅና በማግኘት ቀዳሚው ተቋም ሆኗል።



ይህ ዓለም አቀፍ ሰርተፍኬት ለማዕከሉ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።


የISO 21001:2025 እውቅና የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት የአሰራር ሥርዓት እና የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት የሚያሟሉበት መንገድ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድን የጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ መመዘኛ ነው። 


የISO 21001:2025 ሰርተፍኬት ተቋሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሥልጠና ጥራት፣ የባለድርሻ አካላትን እርካታ ያረጋገጠ ተገልጋይ ተኮር አሰራር እና ቀጣይነት ያለው የማሻሻል ብቃት እንዳለው የሚያረጋግጥ   ነው።


ስኬቱ ማዕከሉ ለሌሎች ተቋማት አርአያ በመሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራትና የልህቀት ማዕከልነቱን በተጨባጭ ለማስመስከር ያስችለዋል።

ሰርተፍኬቱ ማዕከሉ ላለፉት ዓመታት በአሰራር፣ በሰው ኃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ሲያደርግ የቆየው ከፍተኛ ጥረት ውጤት ነው።  እውቅናው ተቋሙ ወደፊት ለሚሰጣቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች እንዲሁም ለኢንዱስትሪው የሚሰጠው የምርታማነት ማሻሻያ ድጋፍ ትልቅ የሞራልና የሙያ ስንቅ ይሆናል።

‹‹ከፍታን ማጽናት፤ነገን ማላቅ››

ተጨማሪ  መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ  

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@bols20116?_t=ZM-8y9L28EOubG&_r=1
👉Facebook 
https://www.facebook.com/addisababatvetbureau
👉Telegram 
https://t.me/AABOLS
👉YouTube 
https://youtube.com/channel/UCvdSuxRP-cMVC7-lSv2fxag?si=YiWZURWWlmGDBPjv

👉website 
https://aabols.gov.et

👉ለቅሬታ፣ አስተያየትና ጥቆማ
https://complain.aabols.gov.et

👉ለነፃ የስልክ ጥሪ
6524
.

Copyright © All rights reserved.

Created with