Home የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የISO 21001-2025 የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተረከበ።

የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የISO 21001-2025 የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተረከበ።

15th October, 2026

🇪🇹 ጥቅም 2/2019 ዓ.ም 🇪🇹

በአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የISO 21001-2025 የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በይፋ ተረክቧል።

የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ እውቅናው ማዕከሉን ተፎካካሪ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የማርኬቲንግና ቢዝነስ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተኬ ብርሃነ በበኩላቸው ዕውቅናው ማዕከሉ ላሳየው የጥራት፣ የብቃት፣ የተቋማት ትጋት እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም ዕውቅናው የተጠቃሚዎችን እርካታ በማሳደግ፣ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት በማሳደግ እንዲሁም በውጤት ላይ የተመሠረተ አመራር እንዲኖር ያስችላል ብለዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ በዕውቅና ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የ ISO ታስክ ፎርስ አባላትን ጨምሮ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት የምስጋናና የዕውቅና መርሀ ግብር ተካሂዷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://aabols.gov.et/qr.html

.

Copyright © All rights reserved.

Created with