ለመላው የቴክኒክና ሙያና የማዕከላችን ማህበረሰብ እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
ማዕከላችን በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው 5ተኛው የ ASEB AWARDS 2026 (Africa Startup Ecosystem Builders Summit & Awards) የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ "Coworking Space Champion of the Year 2026" በመባል የዘመኑ የላቀ አሸናፊ በመሆን የተሸለመ ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ አንደኛና ብቸኛ ተወካይ በመሆን ከአፍሪካ ቀዳሚውን ስፌራ በመያዝ አሸናፊ ሆኗል።
ሽልማቱ የ ASEB Society መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ማክኬቪን አያባ (McKevin Ayaba) በተፈረመ የምስክር ወረቀት የተረጋገጠ ሲሆን፣ ማዕከላችን ለስራ ፈጣሪዎች ተገናኝተው በጋራ የሚያድጉበት ምቹ የመስሪያ ቦታና ማህበረሰብ (Coworking Space) በመፍጠር ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተበረከተ ነው።
ይህ ታላቅ ድል እንዲመጣ በድምጽ መስጫ ስነ-ስርዓቱ ላይ በንቁ ተሳትፎ ያደረጋችሁ በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ውጤቱ የጋራችን ነውና እንደገናም እንኳን ደስ አላችሁ!
የልህቀት ማዕከሉን የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Websit .... https://pice.sims.aatvetb.edu.et/
Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)
Facebook Channel ………….PICE (https://m.facebook.com/edu.pice.et/)
TikTok Channel ………Pice_1962 (https://www.tiktok.com/@pice_1962)
.