Home "TVET Transformation For Excellence And Sustainable Development"

"TVET Transformation For Excellence And Sustainable Development"

22nd October, 2026

«የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ለላቀ ውጤትና ለዘላቂ ልማት» በሚል መሪ ሐሳብ ዓመታዊ የምርምር ኮንፈረንስ ተካሄደ።

ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም
«የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ለላቀ ውጤትና ለዘላቂ ልማት» በሚል መሪ ሐሳብ ዓመታዊ የምርምር ኮንፈረንስ የተካሄደ ሲሆን ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ከኢትዮጵያ ቴክኒካል ልህቀት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን አዘጋጅተዋል።

መርሃ ግብሩን አስመልክቶ የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ለተጋባዥ እንግዶችና ለተሳታፊዎች አድርገዋል።

በተጨማሪም ዶ/ር አንማው ታደሰ የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ይህ ጥናትና ምርምር የሀገርን ችግር ከመፍታት አንጻር የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

በዚህ የምርምር ኮንፈረንስ ላይ የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ስልጠናና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ እንዲሁም ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኙዋል።

በቀረበው ኮንፈረንስ ላይ የቀረቡት አራት ዋና ዋና የምርምር ርዕሶች ሲሆኑ

በኢትዮጵያ የሙያ ትምህርትና ስልጠናን በተመለከተ ያለውን የህዝብ አመለካከት ማሻሻል

የሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ዘርፍ ዲጂታል ሽግግርን መምራት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ያለው የተቋማዊ ክትትል አሠራር ሁኔታ

በኢትዮጵያ የሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ዘርፍ ዲጂታል አመራርና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዘ የአረንጓዴ ክህሎቶች (Green Skill) ማዳበር በሚሉ ርዕሶች ላይ ጥናታቸውን አቅርበዋል።


ይህ የምርምር ኮንፈረንስ የሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፉን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ (ዲጂታል ሽግግር እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ጋር በማስተሳሰር፣ የህዝብ አመለካከትን በማሻሻል፣ የክትትልና ቁጥጥር አሰራሮችን በማጠናከርና በማዘመን እንዲሁም ለአረንጓዴ ልማት የሚጠቅሙ ክህሎቶችን በማዳበር ረገድ ለሀገር አቀፍና ለከተማዋ የዘላቂ ልማት ስኬት ወሳኝ ግብዓቶች እንደሚሆኑ ተገልጿል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/@pice1962)

Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/@pice_1962)

.

Copyright © All rights reserved.

Created with