Home (#ትስስሩ_ህዝብና_መንግስት_የሰጠንን_ሀላፊነት_በብቃት_ለመወጣት_ቃል_የምንገባበት_ነው) #ክቡር_አቶ_ጥራቱ_በየነ

(#ትስስሩ_ህዝብና_መንግስት_የሰጠንን_ሀላፊነት_በብቃት_ለመወጣት_ቃል_የምንገባበት_ነው) #ክቡር_አቶ_ጥራቱ_በየነ

01st August, 2025

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅዱን ለተጠሪ  የክፍለ ከተማ ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤቶችና ለቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች   በማስተዋወቅ የትስስር ሰነድ ተፈራርሟል።

ቢሮው በዛሬው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ባካሄደው   የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ለ350ሺ ዜጎች ቋሚ  የሀገር ውስጥ የስራ ዕድል በመፍጠር ለ15ሺ ዜጎች የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ለመስጠት አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል።የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አካባቢያዊ የመልማት ፀጋዎችን መሰረት አድርገው ስልጠና እንዲሰጡ በትኩረት እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ  31ሺ 500 መደበኛ ስልጣኝ  እና 350ሺ የአጭር ጊዜ ስልጠና ይሰጣል።

በ2018 በጀት ዓመት ቢሮውን ጨምሮ የተጀመሩ የ10 ኮሌጆች የISO ብቃት ማረጋገጫ  ሰርተፍኬት ባለቤት እንዲሆኑ ይሰራል።በበጀት ዓመቱ 15ሺ አዲስ ኢንተርፕራይዞችን በ105  አንቀሳቃሾች  ለማደራጀት እንሚሰራም ተመላክቷል።

ትስስሩ ህዝብና መንግስት የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት ለመወጣት ቃል የምንገባበት ነው ያሉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ  የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ  ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተጠሪ ተቋማቱ በትኩረት መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ዘገባው የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው

.

Copyright © All rights reserved.

Created with