ማዕከሉ ከልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ10 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው ዕለት የፍሳሽ ማስተላለፊያ ትቦዎችን የማፅዳት ስራ ሰርቷል፡፡
በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት የማዕከሉን የወርኃዊ ጽዳት ዘመቻ ያበረታቱት የወረዳው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ወቅቱ ክረምት እንደመሆኑ መጠን የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦዎችን ከደረቅ ቆሻሻ ነፃ ለማድረግ እንደከተማ በንቅናቄ እየተሰራ እንዳለ ያመላከቱ ሲሆን በዚህም የምርታማነት ግቢ ካለው የጽዳት ዘመቻ ልምድ አንጻር ጥሩ የሚባል ስራን እየሰራ እንደሆነና በዚህም ምስጋና እንደሚገባው ገልፀዋል ፡፡
ነሃሴ 2/2017ዓ.ም
ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል













.